Home > Uncategorized > ስምንት ጊዜ ባንዲራዋን የቀያየረች ሀገር “ኢትዮጵያ”

ስምንት ጊዜ ባንዲራዋን የቀያየረች ሀገር “ኢትዮጵያ”

ስምንት ጊዜ ባንዲራዋን የቀያየረች ሀገር “ኢትዮጵያ”

(አንድ አድርገን ጥቅምት 26 2005 ዓ.ም)፡-  ኢትዮጵያ ዘመን ተሻጋሪ የሰንደቅ አላማታሪክ ካላቸው ሃገራት መካከል አንዷ ናት  ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እስከ 1890ዎቹሁለተኛ አጋማሽ ድረስ በቀለማትም አንድ ወጥ አልነበረም ፤ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ያሉት ሰንደቅ አላማ ቀለማት ወጥነት ባለው በተያያዙ አራት ማእዘናትበጥቅም ላይ የዋሉት በ1890ዎቹ መጨረሻ ነው ፤ በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሰንደቅአላማ ልዩ ትርጓሜና ስርፀት የተሰጠው በ1898 እንደሆነ ይነገራል ፤ ቢጫ የብርሃን፣ ቀይየመስዋዕትነትና አረንጓዴ የተስፋ ምልክት ተደርጐ ይወሰዳል፡፡  ከዚህ በኋላ ሰንደቅአላማችን አንድ ጊዜ መንፈሳዊ ሌላ ጊዜ ፖለቲካዊ ትርጓሜ እየታከለበት ዘመንተሻግሯል ፤  እኛ ኢትዮጵያውያን በሰንደቅ አላማችን ስም በጐም ሆነ መጥፎ ተግባራትበተፈፀሙባቸው ዘመነ መንግስታት ጭምር ለሰንደቅ አላማችን ያለን ፍቅርና ክብርእጅግ ጥልቅ ነው ፤ ጥንታውያን ጀግኖች ወላጆቻችን ሰንደቅ አላማችንን ይዘው አስደናቂትግልና ውጊያ በማካሄድ ከባዕዳውያን ቀጥተኛ ተፅዕኖ ነፃ የሆነች ሃገር አስረክበውናል ፤ በአንዲት ባንዲራቸው ጥላ ስር በመሆን ወራሪውን ሃይል በእግዚአብሔር ረዳትነትና እና በታማኝ አርበኞች ጀግንነት ከቀኝ ግዛት ነጻ የሆነች ሀገር አቆይተውልናል ፡፡
ኢትዮጵያውያን ለአያሌ ዘመናት ብሔራዊ ክብራችንን ባዋረደና እንደ ህዝብአንገታችንን ባስደፋን አስከፊ የድህነት ማቅ ውስጥ ኖረናል ፡፡ አሁን ሰንደቅ አላማችን የጭቆናም የጭፍጨፋ  አርማ አይደለም።  የሰንደቅ አላማችን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት እንደ ዱሮው ሁሉ የልምላሜ የተስፋና ለነፃነት የሚከፈል መስዋዕትነት ምልክቶቻችን ናቸው ። 
“አፍ ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም” እንደሚባለው ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አውቀው ይሁን ሳያውቁ “ባንዲራ ጨርቅ ነው” በማለት በአደባባይ ሲናገሩ ጆሯን ሰምቷል አይናችንም አይቷል ፤ በዚህ ንግግራቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን የባዲራው ነገር የገባቸው እጅጉን ውስጣቸው ተጎድቷል ፤ እድሜ ልካቸውን ለሀገር ብለው ከጠላት ጋር ጦር ሜዳ ለተዋደቁ አባቶቻችን ይህ አባባል አጥንት ዘልቆ የሚሰማ ስሜት ፈጥሮባቸው አልፏል ፤ አሁንም ጥቂቶች ይችን አባባል በመያዝ የፖለቲካ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚሯሯጡ ኃይሎች አልጠፉም ፤ አቶ መለስ ይህን በተናገሩ በሳምንታት ውስጥ አፋቸውን ሞልተው “ይቅርታ መናገር አልነበረብኝም ተሳስቻለሁ” የማይሉ ሰው ስለሆኑ ምን ማለት እንደፈለጉ በሌላ አባባል ንግግራቸውን መስመሩን ማስቀየር ችለው ነበር ፡፡
የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ቀን በዓል መከበር የጀመረው በአዲሱ ሚሊኒየም መጀመሪያ ላይ ነው ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀው የሰንደቅ አላማ አዋጅ በዓሉ በየአመቱ በመስከረም ሁለተኛ ሳምንት ሰኞ እንዲከበር ይደነግጋል ፤ አዋጁ መስከረምን የመረጠው ወሩ ለሃገራችን የዘመን መለወጫና አዲስ የተስፋ የስራና የለውጥ መንፈስ የሚፈጠርበት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ይመስላል ፤  ለዘመናት  ባንዲራ ያላት ሀገር  ለ5ኛ ጊዜ በአሉን ባለፈው ሳምንት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፤ የመከላከያ ሰራዊት ፤ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ፤ ጀግኖች የኢትዮጵያ አባትና እናት አርበኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲየም ጥቅምት 19 2005 ዓ.ም ተከብሯል፡፡

የሰንደቅ አላማችን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ህብረ-ቀለማት ያለፈውም ሆነ የመጪው ጊዜ በልማት የመለወጥ ፣ በነፃነትና በተስፋ የመኖር ራዕያችን አሻራዎች ናቸው፡፡ የአግድም ቀለሞች አረንዴ- ስራ፣ ልምላሜና እድገት  ፤ ቢጫ -የተስፋ፣የፍትህና የእኩልነትቀይ- ለነጻነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕትነትና የጀግንነት ምልክት ነው፡፡ ይህን የቀለም ህብረት ኢትዮጵያ መጠቀም የጀመረችው ከአድዋ ጦርነት በፊት መሆኑን ታሪክ ይናገራል ፤ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ይህን የቀለም ህብረት መጠቀም የጀመሩት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ ይታወቃል ፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነትና የቅኝ አለመገዛት ተምሳሌት የሆነች ሀገር በመሆኗ በርካቶች ይህን ለመጠቀማቸው ቀዳሚ ምክንያን  መሆኑን የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ፡፡
በአሁኑ ሰዓት መንግስት ከዚህ በፊት ለባንዲራ የነበረውን ዝቅተኛ አመለካከት በመተው በአመት አንድ ቀን የባንዲራ ቀን ብሎ ማወጁ የሚያስመሰግነው ተግባር ነው ፤ ከዚህም በተጨማሪ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ፤ የግልና የመንግስት ሰራተኖች ዘንድ እና ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ የባንዲራ ቀን መከበር መቻሉ ጥሩ ነው የሚል አስተያየት አለን፡፡  

በተለያዩ ጊዜያት በሃገራችን የነበሩ የሰንደቅ አላማ ምስሎችን እንደሚከተለው እንመልከት 

ይህ ኮከብ ምንድነው? please click here: http://en.wikipedia.org/wiki/Satanism
አሁን የኢፌድሪ መንግስት የሚጠቀምበት ባንዲራ ላይ መሀሉ ላይ የተቀመጠው ኮከብ ፤ ቀለምና መግለጫ የተለያዩ አመለካከቶች በተለያዩ የህብረተሰቦች ዘንድ ሲንጸባረቅ ይታያል ፡፡ ኮከቡንና ፤ የሚያቋርጠው መስመር  ምን ማለት እንደሆነ በተለያዩ አመለካከቶች ይገለጻል፤ መንግስት የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነትን የሚያንጸባርቅ መሆኑን ሲናገር ሌሎች ደግሞ ፍጹም የሆነ ስህተት ነው በማለት አስተያየታቸውንበመስጠት ኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ ያለውን ኮከብ Satanism ጋር ግንኙነት እንዳለው ያትታሉ፡፡
 pentagram is often used to represent Satanism.
Satanism is a broad term referring to a group of Western religions comprising diverse ideological and philosophical beliefs. Their shared features include symbolic association with, or admiration for the character of, Satan, or similar rebellious, promethean, and, in their view, liberating figures.
Satanist groups that appeared after the 1960s are widely diverse, but two major trends are Theistic Satanism and Atheistic Satanism. Theistic Satanists venerate Satan as a supernatural deity. In contrast, Atheistic Satanists[2] consider themselves atheistsagnosticsignostics or apatheists and regard Satan as merely symbolic of certain human traits. This categorization of Satanism (which could be categorized in other ways, for example “Traditional” versus “Modern”), is not necessarily adopted by Satanists themselves, who usually do not specify which type of Satanism they adhere to.[citation needed] Some Satanists believe in a god in the sense of a Prime Mover but, like Atheistic Satanists, do not worship it, due to the deist belief that a god plays no part in mortal lives.
በዚህ ላይ እርስዎ ምን ይላሉ? 
እውን ይህ ኮከብ ትክክለኛው ትርጓሜ መንግስት እንደነገረን ነውን ?
Advertisements
Categories: Uncategorized
  1. No comments yet.
  1. No trackbacks yet.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: