Home > Uncategorized > የመጨረሻ ምክር ለሽማግሌው ስብሃት ነጋ

የመጨረሻ ምክር ለሽማግሌው ስብሃት ነጋ

የመጨረሻ ምክር ለሽማግሌው ስብሃት ነጋ


By: Asress M.

ከጥላቻ ጋር በፍቅር የሰከሩት አቶ ስብሃት የመሃይምነት-ድፍረት ንግግራቸውን መቸ እንደሚያቆሙ ማወቅ አልተቻለም:: ባለፈው ሳምንት ጀርመን ፓርላማ ድረስ ሄደው “የኢትዮጵያ ህዝብ ስርአት የሌለው እና ለዲሞክራሲ ብቁ ያልሆነ“ በማለት ወርፈውት ተመልሰው ነበር:: እኔም በግሌ ይህ አይነቱ ንግግር የመጨረሻው የመሃይምነት ድፍረት መሆኑን በመጠቆም ሽማግሌው በካይ የሆነ ንግግራቸው ለመተው ወይ ከመጽሃፍ ውይ ከእድሜ እንዲማሩ እንምከራቸው በማለት ጽፌ ነበር:: ጥጋበኛው ሰውየ እንኳን ምክራችን ሊሰሙ ይግረማችሁ በማለት በተከታታይ ላለፉት 20 ዓመታት ሲያንቋሽሹት በነበረው በአማራው ህዝብ ጥላቻቸው ሳያቆም በቅርቡ የደቡብን ህዝብ “ራቁቱን የሚሄድ“ በማለት ወርፈውታል:: ይህ የሚያሳየው አቶ ስብሃት በትግራይ ህዝብ ስም ቁማር መጫውቱን አጠናክረው መቀጠላቸውን ነው:: ምስኪን የትግራይ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ሆኖ ለሃገር ሉአላዊነት እና ለነጻነት መስዋእትነት እንዳልከፈለ አሁን በነ ስብሃት አይነት ግለሰብ መወከሉ ያሳዝናል:: በተጨማሪም ሰሞኑን አቶ ስብሃት የኤርትራ መሬቱ ሳይሆን ህዝቡ ነው የኛ ብለው ነበር:: መልካም ነው የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም ወገኑ የሆነውን የኤርትራን ህዝብ ይቅርና ከየትም ክፍለ አህጉር የመጣን ህዝብ አክብሮ ተቀብሎ አብሮ በመኖር የሚታወቅ ነው::
ለዚህም ናዚዎች ወደ አገራቸው ተሰደው የመጡትን የእስራኤል ፈላሻዎች ለማጥፋት ሌት ተቀን ሲሞክሩ ውዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን የእስራኤል ፈላሻዎች እና የነብዩ መሃመድ ቤተሰብን አክብሮ ተቀብሎ አብሮ በመኖር ታላቅነቱን አሳይቷል :: ነገር ግን ለምን አቶ ስብሃት ለህዝብ የሚቆረቆሩ ከሆነ አማራውን ኦሮሞውን እና ደቡብን ይጠላሉ? አቶ ስብሃት ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ከሚያውሩን ስለሚያውቁት ስለራሳቸው እና ስለ ቤተሰባቸ ታሪክ ቢያወሩን ይሻል ነበር::
እኔ የሚገርመኝ አቶ ስብሃት እና መሰሎቻቸው የሚያስተዳድሯትን አገር ኢትዮጵያን የሚጠሉት ለምንድን ነው? ከዚህ በፊት አቶ መለስ “ሱዳኖች የኢትዮጵውያኖችን ስርአተ አለበኝነት ታግሰው ነው የኖሩት“ ብለው የኢትዮጵያን ህዝብ ወርፈውት ሳያበቁ ጋሻ መሬት ቆርሰው ሰጡ:: እስኪ አሁን ሱዳኖች ለኢትዮጵያውያን በጎ አሳቢዎች እና ደጎች መሆናቸውን አሁን የተጀመረውን የባይን ግድብ እና ወደፊትም ሌላ ግድብን እሽ ብለው ሲያስገድቡን እና ሲተባበሩን እናያቸው አይደል:: መሪዎቻችን ግን ምን ቢነካቸው ነው እንደዚህ በጥላቻ የተበከሉት? ባለፈው ሳምንት ከሰማንያ ሚሊየን ኢትዮጵያዊ ውስጥ እንደ ስብሃት ነጋ ያልሰለጠነ እና ከዘመኑ ጋር የማይራመድ ሰው የለም በማለት ጽፌ ነበር:: ምክንያቴም ግልጽ ነው::
አቶ ስብሃት ነጋ ባለፉት 20 አመታት የአማራን ህዝብ እና ከዚህ በፊት በስሙ ይነግዱ የነበሩትን የገዥ መደቦች ሳይለዩ ባጠቃላይ ህዝቡን ለማንቋሸሽ እና ለማዋረድ በተለያየ ግዜ ያደረጉትን በካይ ንግግሮች በመዘርዘር ነበር:: አሁንም አቶ ስብሃትን ደጋግሜ የምነግራቸው ነገር ቢኖር በመጀመሪያ የአማራውን ህዝብ ከደቡብ ከትግራይ እና ከኦሮሞው ህዝብ ጋር ለማጋጨት የሚያደርጉትን የተለመደ ሴራ እንዲያቆሙ ሁለተኛ ባጠቃላይ ህዝብን መናቅ እና በማናለብኝነት መውርፍን እንዲያቆሙ እና ቢያንስ የቀራቸውን ጥቂት ቀን ስለ መፈቃቀር መከባበር ስለ እውነተኛ የሃብትና የስልጣን ክፍፍል ተናግረው እንዲያልፉ ነው::

Advertisements
Categories: Uncategorized
  1. No comments yet.
  1. No trackbacks yet.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: