Home > Uncategorized > የጎሳ ፌዴራሊዝም ከእውነተኛ ፌዴራሊዝም ጋር ምን አመሳሰለው?

የጎሳ ፌዴራሊዝም ከእውነተኛ ፌዴራሊዝም ጋር ምን አመሳሰለው?

የጎሳ ፌዴራሊዝም ከእውነተኛ ፌዴራሊዝም ጋር ምን አመሳሰለው?

By: Asress M.

ይህንን አጭር ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ተስፋየ ሃቢሶ የተባሉ (በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩ) ግለሰብ ስለ የጎሳ ፌዴራሊዝም (Ethnic federalism) በ Trgrai Online ድረ ገጽ ላይ የጻፉትን የእንግሊዘኛ ጽሁፍ በማንበቤ ነው:: ጽሁፉ በግምት ወደ ስድስት ገጽ ይሆናል:: በጣም የሚገርመው አንድም ሳይቀየር እያንዳንዱን ቃል እና አረፍተ ነገር ከተለያዩ ድረ ገጾች እና መጻህፍት የወሰዱ ሲሆን ለተወሰኑት ሃሳቦች ማጣቀሻ (Reference) ሲሰጡ አብዛኛውን የጽሁፉ ክፍል የራሳችው በማስመሰል ማጣቀሻ ሳይሰጡ ቢያንስ እንኳ በራሳቸው ቃል እና አገላለጽ ለመጠቀም ሳይሞክሩ እንዳለ Copy paste በማድረግ ከዚህ በፊት የለመደባቸውን ስርቆት (Plagiarism) አጠናክረው ገፍተውበታል:: የግለሰቡን የከዚህ በፊት ስርቆት (Plagiarism) ማየት የፈለገ ሰው ስማቸውን ጎግል ላይ ጽፎ ፈልግ የሚለውን ቢጫን ይጎለጉልለታል::
የጽሁፋቸው ጭብጥ
የጎሳ ፌዴራሊዝም ስኬትን በተለይም ካናዳን እና ስዊዘርላንድን በተጨማሪም በጥቂቱ የህንድን በቅርቡ ደግሞ የቤልጅየምን ልምድ እየጠቀሱ የጎሳ ፌዴራሊዝምን ስኬት ጉዞ ለመግለጽ ይሞክራሉ:: ቀጥለውም የጎሳ ፌዴራሊዝም በታትኖ የጣላቸውን የቀድሞዋን ዩጎዝላቭያ ችኮዝላቫኪያ እና ሶቬት ህብረትን እንዲሁም ሌሎች ሃገራትን የተበታተኑበት ምክንያት እንደ ኢትዮጵያ እውተተኛ የጎሳ ፌዴራሊዝምን ስላልተገበሩ እና ዲሞክራሲን ባለማስፈናቸው ነው ይሉናል:: በመጨረሻም የጎሳ ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ ውስጥ መስራት አለመስራቱ ገና ያልተረጋገጠ እና በደንብ ያልተፈተነ በመሆኑ ልንታገስ እና ልንሞክረው ይገባል ይሉና ይደመድማሉ::
እውነታው
አቶ ተስፋየ ሃቢሶ የጠቀሷቸው ካናዳና እና ስዊዘርላንድ የሚከተሉት ፌዴራሊዝም የኢትዮጵያ መንግስት እየተገበረ ካለው የጎሳ ፌዴራሊዝም በጣም የተለየ ነው:: ካናዳና እና ስዊዘርላንድ የሚከተሉት ፌዴራሊዝም multi-national federalism በመባል የሚታወቅ ሲሆን በተቃራኒው የኢትዮጵያ መንግስት እየተገበረ ያለው Ethnic federalism በመባል ይታወቃል:: ልዩነቱን ባጭሩ ለማስቀመጥ የኢትዮጵያ መንግስት እየተገበረ ያለው የጎሳ ፌዴራሊዝም (Ethnic federalism) ዋና መርሁ ክልሎችን ሲከልል የቋንቋን እና የባህልን እንዲሁም የጎሳ (ዘር) ልዩነትን መሰረት ባደረገ መሆኑና ልዩነቱን የበለጠ በሚያባብስ መልኩ ሁሉኑም የኢኮኖሚ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ተቋማት ሲያቋቁም እንደዚሁ በጎሳ (በዘር) በማደራጀቱ ክልሎችን አስተሳስሮ የያዘው ገመድ ወደፊት እየከረረ እየከረረ የመበጠስ አደጋ እንዲገጥመው ማድረጉ ነው:: በተቃራኒው የካናዳና የስዊዘርላንድን ፌዴራሊዝም ስንመለከት እንደ የኢትዮጵያ መንግስት ከላይ ወደታች የሚፈልገውንም የማይፈልገውንም ግለሰብ ዎይም ህዝብ አንተ በግድ ትግሬ ነህ አንተ ደግሞ በግድ አማራ ነህ አንተ ደግሞ በግድ ኦሮሞ ነህ የማይል እንዲሁም እያንዳንዱን የኢኮኖሚ (የተለያዩ የልማት ድርጂቶች) የፖለቲካ (ለምሳሌ የገዥው ፓርቲ አዎቃቃር) እና የማህበራዊ ተቋማትን በዘር መነጽር የማያቋቁም ባጭሩ በፍትሃዊ የስልጣን እና የሃብት ክፍፍል የሚያምኑ የዲሞክራሲ ሃገራት ናቸው:: ይህን ሁሉ ስል ፌዴራሊዝምን ኢትዮጵያ መጠቀም የለባትም ለማለት ሳይሆን እውነተኛ የፌዴራሊዝም መንግስት አወቃቀር በኢትዮጵያ ተተግብሮ ማየት ስለምፈልግ ነው:: እውነተኛ የፌዴራሊዝም መንግስት አወቃቀር በፍትሃዊ የስልጣን እና የሃብት ክፍፍል ስለሚታወቅ ለኢትዮጵያችን ጠቃሚነቱን መገንዘብ አያዳግትም:: የእውነተኛ ፌዴራሊዝም ጥቅሞች እና መገለጫዎች የሚከተሉት ናቸው::
 ስልጣንን እና ሃብትን ከማእከላዊው መንግስት ወደ ከልላዊ መንግስት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በማከፋፈል የህዝቡን የፖለቲካ የቋንቋ የባህል እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመፍታት ይረዳል:: በዚህም መረጋጋትን በማግኘት የአንድ ሃገር ልማት ይፋጠናል::
 ለሁሉም ክልሎች ስልጣን በመስጠት አብዛኛውን ቁጥር የያዘው የህዝብ ወገን አናሳ ቁጥር ያለውን ወገን እንዳይጨቁን ይከላከላል::
 እያንዳንዱ የክልል መንግስት ከየአካባቢው ህዝብ ጋር የተቆራኘ ስለሚሆን የዕለትተለት የህዝቡን ችግር ለመረዳት እና ለመመለስ እንዲችል በማድረግ መንግስትን ለህዝብ የቀረበ ያደርገዋል::
 እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በቆዳ ስፋት ሰፊ ለሆኑ ሃገራት ከአሃዳዊ የመንግስት አወቃቀር ይልቅ ፌዴራሊዝም በክልል መንግስታት አማካይነት ሁሉንም የሃገሪቱ አካባቢዎች ተደራሽነት ያስፋፋል ለመቆጣጠርም ያስችላል::
እውነተኛ የፌዴራሊዝም መንግስት አወቃቀር ለህዝብ ጥያቄዎች እውነተኛ መልስ ይሰጣል በተቃራኒው የኢሃዴግ ቅብ ፌዴራሊዝም (fake federalism) ለሁሉም ክልሎች እውነተኛ ስልጣን እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን ስለማይሰጥ ዋና አላማው ጥቂቶች ብዙሃኑን እየበዘብዙ የሚኖሩበትን መንገድ መፍጠር ነው:: የኛ ኢትዮጵያውያን ዋናው ጥያቄ ፍትሃዊ የሃብት እና የስልጣን ከፍፍል እንጅ የርእዮተ ዓለም ጥያቄ አይደለም:: ፍትሃዊ የሃብት እና የስልጣን ከፍፍል ካለ ዲሞክራሲ አለ:: ስለዚህ ተስፋየ ሃቢሶ የተባሉ ግለሰብ ቀልዱን ትተው ስለ ፍትሃዊ የሃብት እና የስልጣን ከፍፍል መንግስትን እንዲመክሩልን እጠይቀወታለሁ::

Advertisements
Categories: Uncategorized
  1. No comments yet.
  1. No trackbacks yet.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: