Home > Uncategorized > የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት: ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት: ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት
Ethiopian National Transitional Council

ግልጽ ደብዳቤ
ለጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ
ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት
መስከረም 10 2005

በታሪከ አጋጣሚ መልካም ሥራን ሠርቶ ታላቅ ስምን አትርፎ ለማለፍ ዕድሉ
የሚገጥማቸዉ በጣም ጥቂቶች ናቸዉ። በተለይም በሀገር ደረጃ በሚሊዮኖች ህዝቦች
እጣ ፈንታ ላይ መልካም ነገሮችን ሠርቶ የማለፍን ዕድልን የሚያገኙት ደሞ እጅግ
በጣት ሚቆጠሩ ናቸዉ። ሃገራችን ኢትዮጵያ ባሁኑ ወቅት በመስቀለኛ መንገድ ላይ
ትገኛለች፤ በዚህም ወቅት የኢትዮጵያና የህዝቦቿ እጣ ፈንታ በእርስዎ እጅ ወድቋል።
በዚህም የታሪክ አጋጣሚ በመጠቀም የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱንና አንድነቱን ጠብቆ
ቀጣይና ፍትሃዊ ዕድገት የሚያገኝበትን ስርዓት በማመቻቸት ሃገርዎትንና ህዝብዎትን
ይታደጋሉ ብለን እናምናለን። ለዚህም አንደኛዉ አማራጭ በነበረዉ በመቀጠል
አምባገነንነትን፤ ማናለብኝነትን፤ ዘረኝነትን፤ ጭቆናን፤ ሌሎችንም በህዝብና በታሪክ
የሚያስጠይቁ አካሄድን ይዞ መቀጠል። በአንጻሩ ደግሞ ያለፈዉን ለታሪክ በመተዉና
በመዝጋት የተሻለ፤ ፍትሃዊ፤ በመከባበር፤ በመቻቻል፤ በመረዳዳትና፤ በመተባበር፤ ላይ
የተመሠረተ ሁሉን አሰባሳቢ የሆነ የጋራ ሀገርና አስተዳደርን መገንባት ሲሆን፤
ፈረንጆቹ እንደሚሉት ኳሱ በእርስዎ ሜዳ ላይ ነዉ።
አርቆ አስተዋይነትና ክህሎትን በመጠቀም የተሻለዉንና ሁሉንም ወገን የሚጠቅመዉን
አማራጭ ይከተላሉ ብለን እናምናለን። ይህንንም መንገድ የሚመርጡ መሆንዎትን
ለህዝቡ ለማሳየት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለዉጦች በአስቸኳይ በተግባር በማዋል
ለበጎ ጅማሮ ቆርጠዉ መነሳትዎን ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም እንደሚያሳዩ
ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤትም የሚጠበቁት በጎ ጅማሮችዎ
በተለይ ሚከተሉትን እንዲያካትቱ ይጠይቃል።
1. ሁሉንም የፖለቲካ መሪዎች፤ ጋዜጠኞች፤ የሀይማኖትና ሌሎችም በፖለቲካ
አመለካከታቸዉ የታሰሩትን እስረኞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ
እንዲፈቱ። ከእንግዲህም ማንም ኢትዮጵያዊ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት
ለእስርና ሰቆቃ እንዳማይዳረግ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም ይፋ እንዲያደርጉ።
2. የፖለቲካ መቻቻልን ለመፍጠር ሁሉም በሀገር ቤትና በዉጭ በስደት ላይ ያሉ
የፖለቲካ ድርጅቶች ያለምንም ቅድመሁኔታ በነጻነት በሃገራቸዉ ዉስጥ
መንቀሳቀስ የሚያስችላቸዉን ህጋዊ ሁኔታዎች እንዲያመቻቹ።
3. በፖለቲካ አመለካከታቸዉ ምክንያት ከሀገራቸዉ የተሰደዱትንና ከሞት ጀምሮ
የተለያዩ ፍርድ ተፈርዶባቸዉ ከሀገራቸዉ፤ ወገናቸዉና ቤተሰቦቻቸዉ እንዲለዩ
የተደረጉት የሀገራችን ልጆችና ዜጎች ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ
ወደሀገራቸዉ ተመልሰዉ ከቤተሰቦቻቸዉ የመቀላቀል እና ህዝባቸዉንና
ሀገራቸዉን የማገልገል መብቶቻቸዉ ኢንዲከበሩላቸዉ።
4. የጥላቻ ፖለቲካ ቀርቶ በምትኩ ስልጡን የመቻቻል ፖለቲካን ባቀራረብዎ፤
ባነጋገርዎና፤ በሚሠሩዋቸው፤ አርአያነትን የተላበሱ ተግባራት በተጨባጭ
85 S. Bragg Street, Suite 504
Alexandria, VA 22312, USA
Tel: 1-202-735-4262
http://www.etntc.org
contact@etntc.org እንደሚያሳዩ ይጠበቃል። ለዚህም ከሁሉም ተቃዋሚ ወገኖች ጋር ዘላቂና ገንቢ
ሀገራዊ ዉይይት የሚጀመርበትንና ሁሉንም ያካተተና ያሳተፈ ወደ
ዲሞክራሲያዊ የሽግግር ስርዓት ሀገራችን የምትሸጋገርበትን ሁኔታዎች
እንዲያመቻቹ።
5. ሁሉም ኢትዮጵያዉያን በነጻነት የመናገር፤ የመጻፍ፤ የመሰብሰብ፤
ተቃዉሞአቸዉን በሰልፍ የመግለጽና እምነታቸዉን በነጻ የማራመድ
መብቶቻቸዉ መከበራቸዉን በተግባር ያረጋግጡ።
6. የኢትዮጵያ ህዝብ በነፃ የማሰብ፤ የመናገር፤ የመፃፍ፤ የመሰብሰብ፤ የመደራጀት
እና የፖለቲካ ተሳትፎን ለመገደብ ሲባል የወጡት እንደ ፕሬስና ፀረ
ሽብርተኝነት የመሳሰሉት አዋጆችን እንዲሽሩ።
በኛ በኩል ያለንን የመልካም ሀገር ተስፋ ዘርዝረን አስቀምጠናል፡ ይህንኑም
የማስፈጸም የታሪክ ሃላፊነቱ ግን በእርስዎ ትከሻ ላይ ወድቋል። ተግባር የማንነት
መገለጫ ነዉና የለዉጥ ፍላጎትዎን በተግባር ያረጋግጡልናል ብለን በማመን እርስዎ
የሚወስዷቸዉ በሳልና አርቆ አስተዋይነትን የተላበሱ ተግባራት ሁሉንም ወገኖችንና
ህዝባችንን የሚያረካ ዉጤት ለሁላችን እንደሚፈጥር ያለንን ተስፋ በዚሁ አጋጣሚ
እንገልጻለን።
ከሰላምታ ጋር
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት

Advertisements
Categories: Uncategorized
  1. No comments yet.
  1. No trackbacks yet.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: