Home > Uncategorized > የነበረከት ስምኦን አንጃ በአቦይ ስብሃት ላይ የሃያ አራት ሰአት ክትትል እንዲደረግባቸው ለደህንነት መመሪያ ሰጠ

የነበረከት ስምኦን አንጃ በአቦይ ስብሃት ላይ የሃያ አራት ሰአት ክትትል እንዲደረግባቸው ለደህንነት መመሪያ ሰጠ

የነበረከት ስምኦን አንጃ በአቦይ ስብሃት ላይ የሃያ አራት ሰአት ክትትል እንዲደረግባቸው ለደህንነት መመሪያ ሰጠ

ከቅርብ ግዜ ወዲህ በባህሪያቸው የማን አለብኝነትን ባህሪ እያሳዩ የመጡትን አቦይ ስብሃትን የማያቋርጥ ክትትል እንዲደረግባቸው እና ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ በበረከት ስሞን ከሚመራው አንጃ መስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልጠውልናል።

ይህንን በማያያዝም አቦይ ስብሃት ነጋን ያሞጋግሱ የነበሩ ማናቸውም አይነት ጽሁፎችም ሆኑ ቃለመጠይቆች የህውሓት አቀንቃኝና ደጋፊ ከሆኑ ድህረ ገጾች ለይ ተለቅመው እንዲነሱም መመሪያ ተሰጥቷል።

ይህንን በመከተል በአይጋፎረም፣ ትግራይ ኦንላይን እንዲሁም ዋልታ ኢንፎርሜሽን ድህረ ገጽ ላይ በቅርብ ግዜ ተለጥፈው የነበሩ የአቦይ ስብኃት ከቪኦኤ እና ከዶቾቬሌ ጋር እርገዋቸው የነበሩ የአቶ መለስን ጤንነት የሚመለከቱ ቃለምልልሶች መነሳታቸውን ልናረጋግጥ ችለናል በመሆኑም ከአሁን በኋላ ምንም አይነት ቃለ ምልልስ ከማንኛውም ሚዲያ ጋር እንዳያደርጉም ከአቶ በረከት አንጃ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቶአቸዋል።

ከቅርብ ግዜ ወዲህ አቦይ ስብሃት ማንንም ባለመፍራት አቶ መለስንና ሚስታቸውን ጨምሮ ማንኛውንም ሰው በሃይለ ቃል እየዘለፉ እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ሲሆን በተለይ ከአቶ መለስ መሰወር ጋር የሚሰጧቸው ቃለመጠይቆች የተደበቀውን ሚስጥር እንዳይወጣ ሌት ከቀን የሚለፉትን የአቶ በረከት አንጃን ክፉኛ አስቆጥቷል በመሆኑም የአቦይ ስብሃት ነጋን እንቅስቃሴ ከሚታገሱት በላይ ሆኖብናል ይላሉ።

ጥያቄው አቶ ስብሃት ነጋ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ይተገብራሉ ወይስ የሚለው አጓጊ ጥያቄ ሆኖአል? ቀጣይ ሂደቶችንና ክንውኖችን እየተከታተልን እናቀርባለን።

Advertisements
Categories: Uncategorized
  1. No comments yet.
  1. No trackbacks yet.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: