የአሉላ አባ ነጋ ጠላቶች

January 14, 2013 Leave a comment

የአሉላ አባ ነጋ ጠላቶች
አሉላ አባ ነጋ ትግራይ ውስጥ በተንቤን አውራጃ መናዌ በምትባል መንደር እንግዳ ቁቤ ከተባሉ
ገበሬ ነው የተወለዱት።በወጣትነታቸው በሚያሳዩት ጀግንነትየአጼ ዮሃንስን የዚያንጊዜውን ካሳ ምርጫን
ትኩረት ስበው ነበር።
(የቀይ ባህሩ አንበሳ አሉላ አባ ነጋ በጎልማሳነታቸው)
አሉላ በቅድሚያ ጀግነታቸውን ያስመሰከሩት ጉንደትና ጉራዕ በዋለው ጦርነት ለወረራ የመጡትን
ግብጾች ለነጋሪም እንዳይተርፉ ከጨረሷቸው በሁኣዋላ ነው። ከዚህም ድል በሁዋላ በ35 ዓመታቸው ራስ
ሆነው ተሾሙ። የመረብ ምላሽ ገዥም ሆኑ።የአስመራን ከተማም ቆረቆሯትበዚህን ጊዜ ነው። ቁልቁል ወደ
ቀይ ባህር እየተመለከቱም ኢትዮጵያን ለመውረር ለሚመጣ ጠላት ሁሉ መቅሰፍት ሆኑት።
በኩፊት ጦርነትም ማህዲስቶችን ድል አድርገው ለእንግሊዞች በር ከፍተውላቸዋል።(ሁኣላ
ቢክዱንም)በዚህ የተናደዱት አሉላ የእንግሊዙን ተወካይ አውጉስቶስ ዋይልዴን ሲያገኙት “ አገርህ እንግሊዝ
ምን ማለቷ ነው የሄዊትን ስምምነት ጥሳ ጣልያን ያገሬን መሬት ልትወስድ የፈቀደችው? ከቦጎስ የግብጾችን
መከበብ ተዋግቼ ነጻ አላወጣሁም? ከሰላ ላይ ኣስቸጋሪውን ጦርነት አልተጋፈጥሁም? የምችለውን ሁሉ
አላደረግሁም? እናንተ እንግሊዞች እናንተ የምትፈልጉትን ካደረግንላችሁ በሁዋላ
ተዋችሁን(ካዳችሁን)”ሲሉ በንዴት ገልጸዋል። (What does England mean by destroying
Hewett’s treaty and allowing the Italians to take my country from me? …Did I not relieve
the Egyptian garrison in the Bogos country? Did I not fight at Cassala when it was too
late? Have I not done everything I could? You English used us to do what you wanted
and then left us)
ከእንግሊዝ ክህደት በሁዋላ ኢትዮጵያን ሊወር ተጠናክሮ የመጣውን የኢጣልያ ሰራዊት ሰሃጢ ላይ
አድክመው ዶጋሊ ላይ ጨረሱት። በዚህ ጦርነት 400 የጣሊያን ወታደርና 22 መኮንኖችን በመግደል
ጠላትን አሸማቀውታል።
የኢትዮጵያውያን ጀግንነት የታየበትና የጥቁር ዘር ሁሉ የኮራበት፤ የበላይነት የሚሰማቸው የነበሩ
ነጮችም ልካቸውን ያወቁበት ታላቁ የአድዋ ድል ጉልህ ድርሻ የአሉላ አባ ነጋ ነው። ጠርጣራውና
የጠላትን ተንኮል አጥርተው የሚያውቁት አሉላ በሰላዮቻቸው ባገኙት መረጃ ነበር ጣልያን የተፈጠመው።
አዋዕሎምና ጓደኞቻቸው የኢጣልያንን መንቀሳቀስ፣ የመጣበትንም አቅጣጫ፣ የጦሩንም አይነትና መጠን
ለራስ አሉላ መረጃ ሰጡ። እሳቸውም ለአጼ ምንይልክ አስተላልፈው ጣልያንን ራሱ ባጠመደው ወጥመድ
ውስጥ ከተቱት። አውጉስቶ ዋይልድ የሚከተለውን ብሏል ስለ ራስ አሉላ የአድዋ ጦርነት አስተዋጾ።
The Abysssinians never expected to be attacked, and the Italian advance
would have been a complete surprise, had it not been for Ras Aloula, who
never believed the Italian officials, and would never trust them. Two of his
spies observed the Italians leave Entiscio, and arrived by a circuitous route,
and informed Ras Aloula, who was one mile to the north of Adi-Aboona,
that the enemy was on the march to Adowa. The Ras immediately informed
King Menelik and the other leaders, and the Abyssinians prepared for
battle, sending out strong scouting parties in all directions in front of their
positions towards Entiscio.
[11]
During the battle itself, Ras Alula was assigned to watch the Gasgorie Pass
and block the arrival of Italian reinforcements coming from Adi Quala.(አዛውንቱ የአድዋ ጀግና አሉላ አባ ነጋ)
የሰባ ዓመቱ አዛውንት ራስ አሉላ ቁልፍ ቦታ ይዘው ነው ጣልያንን በአድዋ እንዳይተርፍ ያደረጉት።
በተቃራኒውስ ማን ነበር?
ጣልያንማ አገርን ቅኝ ሊገዛ ከሃያላን ፈቃድ አግኝቶ የመጣ የምር የኢትዮጵያ ጠላት ነው።
ዓላማውም ግልጽ ስለነበር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊቋቋመው ቆርጦ ተነስቷል አዛውንቱ ጀግናው አሉላ
አባነጋም ጭምር። ጣልያኖችን በመንገድ መሪነት፣ በሰላይነት፣ ምግብ አብሳይነትን የመሰለ የተዋረደ ስራ
ከማገልገል አልፈው ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻቸውን ጠላት ባስታጠቃቸው መሳርያ ለመቅጠፍ የተሰማሩ
ኤርትራውያንም ሌሎችም ነበሩ። ከጣልያንም በላይ ግን እነዚህ ባንዶች ነበሩ የከፉ የኢትዮጵያ
ጠላቶች።ከነዚህ በዋናነት ከተሰለፉ ከሃዲ ባንዳዎች አንዱ የመለስ ዜናዊ አያት ባሻ አስረስ ተሰማ
በሁዋላም በጣሊያን ደጃዝማች ሆነው የተሾሙ ናቸው።(ለጣልያን አድረው ኢትዮጵያን የወጉ የመለስ ዜናዊ አያት ባሻ አስረስ ተሰማ እኒህ ነበሩ)
ራስ አሉላን የመሰለ የትግራይ ጀግና ፣ እንኒህን የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ጀግና ጠላቶቻቸው
ጣልያኖች፣ እንግሊዞች ሳይቀሩ ከሃኒባል በሁዋላ የተፈጠረ ጀግና ጥቁር ጄኔራል አሉላ ብቻ ነው ብለው
የመሰከሩላቸውን ነው ቆምንለት ለሚሉት የትግራይ ህዝብ ግናና ታሪክ ንቀት ያላቸው የባብዳ ልጆች
በስማቸው የተሰየመን ትምህርት ቤት በሌላው የባንዳ ልጅ ስም የቀየሩት።የህወሃት ካድሬዎች ለመለስ ዜናዊ ሺ ሃውልት መሥራት ይችላሉ። በአሉላ ስም የተሰየመን
ትምህርት ቤት በመለስ መተካት ግን የትግራይን ብሎም የኢትዮጵያን ህዝብ ታሪክ መካድ ብሎም መስደብ
ነው።
አንዳንድ ኤርትራውያን አሉላን ከልብ ይጠሏቸዋል። ቀደም ብሎ በጣልያን መገዛት አሉላ
ስላስቀሩባቸው ሊሆን ይችላል።ከዚያም አልፎ ባንዳ አባቶቻቸውንም ከጌቶቻቸው ጋር ደርበው
ገድለውባቸዋል።
በህወሃት አመራር ላይ ያሉ የኤርትራ ደም ያላቸውና ቁልፍ ስልጣን የተቆጣጠሩ አምባገነኖች በአሉላ፣
በትግራይና አጠቃሎም በኢትዮጵያ ህዝብ ስር የሰደደ ቂም አላቸው። የትግራይን ብሎም ኢትዮጵያን
ታሪክ ለማጥፋት ከዛሬ የተሻለ ጊዜ አያገኙም።
እኛም ኢትዮጵያዊ የምንል ይህችን አገር ለማዳን ከዛሬ የተሻለ ጊዜ የለንም። ነገማ እኛም አገሪቱም
እንደነበርን አንገኝም።
ኢትዮጵያን አግዚአብሄር ይባርካት
አንተነህ መርዕድ

Advertisements
Categories: Uncategorized

What a MANO! A Barefaced Constitutional Violation

December 6, 2012 Leave a comment

What a MANO! A Barefaced Constitutional Violation

By Legesse.T

PM HMD and his comrades are arguing that the country has only one deputy Prime Minister (Demeke) and the government has not violated any constitutional provision. What is their legal authority to say so? It is not just the nomenclature given to the new appointees which has led us all to be skeptical about the new deputies, but the power given to them. It is up to the council of ministers to decide on the organizational structure of ministries and other organs of government responsible to it (Art 77(2) of FDRE constitution). But that doesn’t include reshuffling of constitutionally identified and established offices like the prime minister and the deputy prime minister. Art 74 and 75 have already established these offices and determined their powers. There is one prime minister under Art 74 and one deputy PM under Art 75. It is after launching these two important offices that the constitution left other lower executive organs including ministries and others to be structured by the council of ministers as it wishes as per Art 77(2). We cannot take away a constitutional power from the PM or DPM and assign it to the so called coordinators of the respective clusters in the “Deputy Prime-Minister-ship Position.” If we do so, that would stand against Art 9(3).

The PM himself explained that his direct supervision over the activities of executive organs will be limited to diplomatic, military, security and mega project affairs. This would clearly contradict with Art 74 which has made the PM the “Chief executive’’ and the one who is responsible to follow, supervise and ensure enforcement of the country’s laws and policies in all sectors. This would also have an implication on the powers to be exercised by the deputy PM as he has to act on behalf of the PM in his absence (Art 74(1)).

The Deputy Prime Minister is also assigned to run the social affairs cluster. What does it mean? Is Demeke managing three offices (Acting as a Deputy Prime Minister, Education Minister and Coordinator of his own cluster)? Oh, that might be too much and the same is true when we consider other new appointees. Where is the division of labor then which is an important reason behind the doctrine of separation of power i.e. to bring efficiency? Of course, the government came up with these clusters to ensure efficiency. Let alone the deputy Prime Minister, the PM has gave up (he seems so tired early) and officially admitted that some of his powers will be exercised by the new coordinators. Then, don’t you think that the whole constitutional arrangement is set aside and the new cluster coordinators are now having a power that is even more than what is assigned to the deputy PM under the constitution? Where is their legal authority? Deputy ministership and other lower positions could be given and taken back any time by the government. But, what the government has done is a bit more. I would say it is MANO and needs correction instead of justifying the same. The government has not mentioned a legal basis for its action rather it has made reference to other countries’ executive structures, Ethiopian regional states’ executive organizations and the previous federal government executive arrangements as inputs used by it. All these cannot make the government’s action valid as they will not be above the FDRE constitution (the supreme law of the land).

Categories: Uncategorized

ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች!

November 29, 2012 Leave a comment

ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች!

አቤ ቶኪቻው

አቶ ሃይለማም ሲፈሩ ሲተቡ ቆይተው ዛሬ የካቢኔ ሹመት ለማደረግ ፓርላማ ብቅ ብለው ነበር አሉ። ይዘዋቸው ከመጡዋቸው ካቢኔዎቻቸው መካከል ሌላ ሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ይገኙበታል።

አቶ ሃይለማሪያም ሲያስቡት ሲያስቡት ለአቶ ደመቀ ብቻ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መስጠት አይችሉትም ብለው ሰጉ መሰለኝ…(መሰለኝ ነው ያልኩት) ዛሬ አቶ ሙክታር ከድር እና አቶ ደብረ ፅዮን ገብረሚካኤልን ደጋፊ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው አሹመዋል። በጥቅሉ በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች አሏተው።

እኛ  ሹመቱን ከላይ ከላይ የምናየው የመንግስታችን አድናቂዎች “እሰይ ሀገራችን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እድገት እመርታ አሳየች” ብለን ካገኘን ፅዋ ካጣን ደግሞ ግንባራችንን እያጋጨን ደስታችንን  እንገልፃናል።

የምር ግን አቶ ሃይለማሪያም ያኔ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይሰሩ የነበረ ጊዜ እንደው ሰውየው መለስ ሆነውባቸው “ተሸከሙ” ያሏቸውን ሁሉ “እሺ ጌታዬ” ይሏቸው ነበር እንጂ፤ የጫኑባቸው ሸክም በእጅጉ ከብዷቸው ነበር ማለት ነው!? አዎና ይኸው አቶ ደመቀ ሸክሙን አይችሉትም ብለው የጠረጠሯቸው ከራሳቸው ልምድ ተነስተው አይመስልዎትም!?

ሌላው ጥርጣሬ የኢህአዴግ “ፈላጭ ቆራጮች” (ይሄ “ፈላጭ ቆራጭ” የሚለው ቃል ኢህአዴግ ይፈልጣል ይቆርጣል ብሎ ለማሽሟጠጥ ታስቦ የገባ ቃል አለመሆኑን በቅንፍ አሰውቀን እንቀጥል)  እና የኢህአዴግ ፈላጭ ቆራጮች አቶ ሃይለማሪያምን ለአንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻ አምነው መተው ምቾት አልተሰማቸውም ይሆናል!

ለማንኛውም ዶክተር ቴውድሮስ አድሃኖምን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ዶክተሩ ከጤና ጥበቃ የተነሱት ጤና ስለነሱ ይሁን ወይስ የውጭ ጉዳዩ ስራ ህክምና ስለሚያስፈልገው አልታወቀም። ሲታወቅ እናወጋዋለን!

Categories: Uncategorized

One party and multi-deputy PM system in Ethiopia

November 29, 2012 Leave a comment

One party and multi-deputy PM system in Ethiopia

By Legesse.T

Our government has buried the constitution once and for all. We can’t find a single constitutional provision any where under the FDRE constitution which says the country can have two, three or more deputy prime ministers at a time. Art 9(3) declares that “It is prohibited to assume state power in any manner other than that provided under the Constitution.” The Government’s decision is undeniably unconstitutional and the House of Federation is responsible to proclaim such acts invalid as per Art 9 (1).

Art 9(1)

“The Constitution is the supreme law of the land. Any law,…… or a decision of an organ of state or a public official which contravenes this Constitution shall be of no effect.”

The House of Federation is the constitutional umpire in Ethiopia. The power to interpret the constitution (62(1)) and make decisions on constitutional disputes (83(1)) are given to this house. Opposition parties and members of the EPRDF may bring such a case to the attention of the House of Federation by virtue of Art 37. The House may give a deaf ear to cases like this. But, the illegality of the move by the government should be disclosed to the public through this constitutionally allowed adjudication process.

While having an Ethnic Federal system is so complex and a potential source of conflict, the government is even making things worse by introducing such unwarranted precedent. If this can be done, then who can stop the government from appointing 20 or so deputy prime ministers for each sector? Why we need to have ministers after all if we have many deputy prime ministers to handle different government departments? Does the government know why a country needs to have just one deputy prime minister instead of two or more? Who should represent the prime minister in his absence? All the deputies? What if there exists a dispute over exercise of power among them? Should they (the deputies) wait for a decision on their disagreement before they act? If so, how a system which can create such a gap could be indispensable?

Categories: Uncategorized

የወቅቱ የአገራችን የፖለቲካ ሁኔታና የወደፊት የትግል አቅጣጫ – በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር

November 27, 2012 Leave a comment

የወቅቱ የአገራችን የፖለቲካ ሁኔታና የወደፊት የትግል አቅጣጫ – በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር

መግቢያ

የሁላችንም የረጅም ጊዜ ህልም፣ አንድነትዋ የተጠበቀ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ሁሉም ኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦአቸውን የሚያበረክቱበት ለአገሬ እሠራለሁ ብለው በነፃ አየር የሚተነፍሱበት ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ምህዳር እንዲፈጠር ካሁኑ ጀምረው እንዲታገሉ ሁኔታን መመቻቸት ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህም የፖለቲካ ምህዳሩን ማየትና ወዳለምነው ግብ ለመድረስ የሚረዱንን አቅጣጫዎች መዳሰሱ ጠቃሚ ነው፡፡

ስለአገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ሁላችሁም ታውቃላችሁ፤ ሆኖም የግለሰቦች አረዳድ ሊለያይ ስለሚችል፣ እኔ የራሴን ግንዛቤ ለመግለጽ እሞክራለሁ፡፡

– የኔን ግንዛቤ ስገልጽ የኔን ሃሳብና አመለካከት ብቻ ተቀበሉ ለማለት ሳይሆን ዛሬም ይሁን በቀጣይ በሚካሄዱ ውይይቶች የኔም ግንዛቤና አመለካከት እንደአስተዋጽኦ እንዲወሰድ ምኞቴ መሆኑን ሳልገልጽ አላልፍም፡፡

– ከኔ አመለካከት ጋር የማይስማሙ እንዳሉም እገነዘባለሁ፡፡ በበኩሌ ከኔ ጋር የማይስማሙትን አከብራለሁ፡፡ ሃሳባቸውንና አመለካከታቸውን ባልጋራምና ባልስማ ማባቸው እነሱንም ሆነ ሃሳባቸውን፣ አመለካከታቸውንና አቋማቸውን አዳምጣለሁ አከብራለሁ፡፡ የመረጃ ስህተት ካለ ስህተቴን ለመቀበልና ለማረም ዝግጁ ነኝ፡፡ የኔን ሃሳብ፣ አመለካከትና አቋም የማይጋሩት ግን እንዲያዳምጡኝና እንዲያከብሩልኝ አደራ እላለሁ፡፡

– ስላገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ዛሬ ሁሉንምና ዝርዝሮችን ለመተንተን አይቻልም፡፡ ስለሆነም በኔ እይታ መነካት አለባቸው የምላቸውን አንዳንድ ጉዳዮች ብቻ አነሳለሁ፡፡ የቤቱ ንቁ ተሳትፎ ውይይታችንን ያዳብራል ብዬ አምናለሁ፡፡ ስለሆነም በሠፊው እንድትሳተፉ አደራ እላለሁ፡፡ ይህ የኔ አስተያየት ለውይይታችን መነሻ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

2. የአጋራችን የወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ
2.1 የሕዝብን ሁኔታ፡-

– ህብረሰባችንን ስናይ ብሶተኛና የማጉረመርም ደረጃ ላይ እንጂ ተናድዶ ንዴቱን በእንቅ ስቃሴ ለማሳየት ዝግጁ የሆነበት ደረጃ ላይ የደረሰ አይመስልም፡፡

– ብዙ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ችግሮች አሉበት፡፡ ይህንን ሰቆቃውንና ብሶቱን ያማርራል፡፡

– በይፋና በአደባባይ አይገልጽም፡፡

– ብሶቱ በማጉረምረም ደረጃ የሚገልጽ ነው እንጂ በአጠቃላይ ወደ ሕብረተሰባዊ ንዴት አልተለወጠም፡፡

– ተናጠል ንዴቶች አልፎ አልፎ ቢገለፁም ሠፊና የአጠቃላይ ሕብረተሰቡ አልሆኑም፡፡

– እነዚህ ተናጠልና ትናንሽ ንዴቶች ወደ ተደራጀና የተቀናጀ ሕዝባዊ እምቢተኘነት እና የእምቢተኘነት እንቅስቀሴዎች አልተለወጡም፡፡ በሌሎች አገሮች በዳቦ ወይም በነዳጅ ዋጋ ላይ ትንሽ ጭማሪ ከታየ የህብረተሰቡ ንዴት ይገነፍላል፡፡ በኛ ህዝብ ዘንድ ግን ይህ አይታይም፡፡ ምልክት ከታየም ጥቂት፣ ተናጠል፣ ያልተደራጁና ያልተቀናጁ ናቸው፡፡

2.2 ገዢው ፓርቲ Authoritarian ነው አምባገነን ነው

– ኢህአዴግ ለሕዝብ ፍላጎት ደንታ የማይሰጥ ድርጅት ነው ፡፡

– የሕዝብን ፍላጎት አያዳምጥም፡፡

– ሕዝብ እሱን ብቻ መስሎ እንዲያድር የሚፈልግ ነው፡፡

– ከሀገርና ከሕዝብ ይልቅ ፓርቲውን ያስቀድማል፡፡

– በሕገ-መንግሥቱ የተረጋገጡትንና በአንቀጽ 29፣ 3ዐ፣ 31፣ እና 38 የተዘረዘሩትን መብቶች አፍኖአል፡፡

– ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት ብሎ ህጎችን በማውጣት፣ ሕግን አስከብራለሁ እየለ ሰብአዊ መብቶችን ይጥሳል፡፡

– ዴሞክራሲያዊ ተቋማት እንዳይኖሩ አድርጎአል፣ ሦስቱም የመንግሥት አካላት ለሕዝብ አገልጋዩች ሳይሆኑ የፓርቲው መሣሪያ ሆነዋል፡፡

– ገዢው ፓርቲ ሕገ-መንግሥቱን አያከብርም በሕገ-መንግሥቱ የተከበሩ መብቶች ተግባራዊ ይሁኑ ሲባል አይፈቅድም፡፡ ሕገ-መንግሥቱ የሚሻሻልበትን መንገድ ከመክፈት ይልቅ በሚያወጣቸው ሕጎች በእጅ አዙር ያሻሽላል፡፡ በአሠራሩ የሕገ-መንግሥታዊ አስተሳሰብን ዋጋ አሳጥቷል፡፡

2.3 የፓርቲ ሥርዓታችን ዴሞክራሲያዊ አይደለም

– በሕገ-መንግሥት ቢደነገግም ዴሞክራሲያዊ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ባገራችን የለም፡፡

– እንደሚታወቀው በንጉሱ ዘመን በፓርቲ መደራጀት ክልክል ነበር፡፡

– በደርግ ዘመን በመጀመሪያ ዓመታት ለደርግ ታማኝ የሆኑ ለስሙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቢወለዱም በመጨረሻ ግን አገሪቱ በአንድ ፓርቲ ብቸኛ ሥርዓት (ኢሠፓ)ሥር ወደቀች፡፡

– ኢህአዴግ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ይመሠርታል ተብሎ ቢጠበቅም እሱ ግን የአውራ ፓርቲን ሥርዓት የሚከተል ሆነ፡፡

– ይህም አውራ ፓርቲነት እንደ አሜሪኮና እንደ ታላቋዋ ብርታንያ ዴሞክራሲያዊ የሆኑ የሁለት ፓርቲዎች አውራነት ቢሆን ባልገረመን፤ ወይም እንደ ጃፓንና እንደ እነ እስራኤል ዴሞክራሲያዊና መድብለ ፓርቲ ሥርዓት በሰፈነበት አውራ ሆኖ ቢወጣ እንቀበል ነበር፡፡ እርሱ ግን በአስገዳጅነት አንድ አውራ ፓርቲ ሆኖ ሌሎች ግን እንደ ጫጩት እንኳ እንዳይኖሩ አድርጓል፡፡

– እሱን የሚገዳደሩ ጠንካራ ፓርቲዎች እንዳይኖሩ በሙስና አሠራር በ Patronage እና በልዩ ልዩ ተጽእኖ ለማዳ ያደርጋቸዋል ወይም ከነጭራሸ እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡

2.4 ብልሹ የምርጫ ሥርዓት አለን

– የምርጫ ሥርዓታችን ለአገራችን ውስብስብ ሁኔታ ምቹ አይደለም፡፡ ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች፣ ብዙ ኃይማኖቶችና የተለያዩ ርዕዩተ ዓለመች ባሉበት ሀገር አሸናፊው ሁሉን የሚወስድበት (First-Past-the Post) ሥርዓት አይመችም ፡፡

– ማህበረሰባዊ ውክልና፣ ተጠያቂነት እና አሳታፊነት (Participatory) መርህን የተከተለ የተመጣጠነ Proportional ሥርዓት እንዲኖር አይፈለግም፡፡

– ይባስ ብሎ በምርጫዎች መሀከልና በምርጫዎች ወቅት ያለው የፖለቲካ ሜዳ (ምህዳር) የተስተካከለ አይደለም፡፡ ዴሞክራሲያዊ ፍትሐዊና ነፃነት የተሞላበት አይደለም፡፡

– በዚህ የምርጫ ሥርዓት ውስጥ ተሸናፊ ፓርቲዎችን የሚመርጥ ብዙ ሚሊዮን የሕዝብ ክፍል በፖርላማ ደረጃ ድምጽ አልባ ይሆናል ማለት ነው፡፡

2.5 የፖለቲካ ልዩነቶች /ችግሮች አፈታታችን ልምድ መፍትሔ ሰጪ ሳይሆን የሚያባብስ ነው

– ባገራችን የፖለቲካ ችግሮች የሚፈቱት በሠላማዊ መንገድ በውይይትና በድርድር ሳይሆን፤ በአስተዳደራዊ፣ ወይም በጉልበት ነው፡፡

– ብዙውን ጊዜ በግለሰቦችና በድርጅቶች ዘንድ ህዝብንና ሀገርን ከማስቀደም ራስን ማስቀደም ይታያል፡፡

– በግለኝነት (የራስን ፍላጎት ማስቀደም) ላይ የተመሠረቱ ልዩነቶችን፣ (የሥልጣን ፍላጎት፣ ለራስ ዝና፣ ገንዘብ/ሀብት ለማግኘት) መፍታት በጣም አስቸጋሪ ናቸው፡፡

– ያገራችን የፖለቲካ ኃይሎች ልዩነቶችን ለመፍታት፤ የሕዝብ ወሳኝነትን ለመቀበል አይፈልጉም፡፡ ህዝብ ፡-

– በምርጫ፣ ወይም

– በህዝበ ውሳኔ፡፡ (Referendum) ችግሮችን እንዲፈታ አይፈለግም፡፡

– ብዙውን ጊዜ ውይይቶች/ ድርድሮች የሚፈርሱት ተደራዳሪዎች

ቅድመ ሁኔታዎችን ስለሚያስቀምጡ ነው፡፡

– ለህዝብና ለሀገር ጥቅም ሲባል ሠፊና ሀገራዊ የትብብር መድረክ ለመፍጠር ፈቃደኝነትና ዝግጁነት ደካማነው፡፡

– በፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድ የተለመደው በአሸናፊነት የማንበርከክ ፍላጎትና የበላይነት ማስፈን አካሄድ ነው፡፡ እምቢ ከተባለ ደግሞ ለመጥፋትም መንቀሳቅ አለ፡፡

2.6 የሠላማዊ ትግል ስልቶችን መጠቀም አልተጀረም

– ሠላማዊ ትግል Passive መሆን አይደለም፡፡ ሠላማዊ ትግል በእንቅስቃሴ የተሞላ ትግል ነው፡፡

– ሠላማዊ ትግል፣ ኃይል/ጉልበት አልባ፣ ህጋዊ፣ ህገ-መንግሥታዊና ዴሞክራሲያዊ ነው፡፡ ሌላን ለመጉዳት /የታለመ አይደለም፡፡

– ሠላማዊ ትግል አንዳንድ ውሳኔዎች፣ አንዳንድ ሕጎችና አንዳንድ ተቋማት የራስን ወይም የሌላን ሰው መብቶች የማነኩ ከሆነ ለነዚህ ውሳኔዎች፣ ሕጎች፣ ወይም ተቋማት እምቢ ማለትንና ያለመታዘዝን ያካትታል /የሚጠይቅ ነው፡፡

– ሠላማዊ ትግል ዜጎች ባለመታዘዝ፣ ለመከላከያነት የሚጠቀሙበት የተቃውሞ መሣሪያ ነው እንጂ የነውጥ ወይም የአመጽ መሣሪያ አይደለም፡፡

– የሠላማዊ ትግል ዓይነቶች ብዙ ናቸው፡፡

ለምሳሌ ያህል፡- የአዳራሽ ወይም የአደባባይ ስብሳዎች፣ Sit-ins፣ አድማ/መታቀብ Boycott (ሥራ፣ ትምህርት፣ ግዥ፣ ምርጫ) እና ሰልፍ የተለመዱ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ባገራችን ተግባራዊ እየሆኑ ያሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

– ሠላማዊ ትግል ሠፊ የመደራጀት፣ የዝግጅት ሥራን ይጠይቃል፡፡

2.7 ውጫዊ ኃይልን የመጠበቅ ልምድና ባህል የተንሰራፋበት አገር ውስጥ ነን

– ለችግሮች መፍትሔ መለካታዊ ኃይልን መጠበቅ አለ፡፡

– ዜጎች ለራሳቸውና ለሌሎች ዜጎች መብቶች መከበር በራስ ከመታገል ይልቅ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ይጠብቃሉ፡፡

– ከግለሰቦችም ፈውስ የመጠበቅ አዝማሚያም ይታያል፡፡

– የውጭ ኃይሎች (መንግሥታት) ችግሮቻችን ይፈቱልናል ብሎ መጠበቅም አለ፡፡

– ይህ ሁሉ መንም ውጤት እንዳላስገኘ መላልሰን አይተናል፡፡

3. የወደፊት ትግላችን አቅጣጫ ምን መሆን አለት፣

3.1 ህዝብን ለለውጥ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ፣

– የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በስፋት መሠራት አለባቸው፡፡

– የመረጃ መስጫ ዘዴዎች መጠናከርና መስፋት ይኖርባቸዋል፡፡ (ለምሳሌ ዘመናዊ/ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን)

– በሕዝብ ውስጥ የማደራጀትና የማቀናጀት ሥራዎች መሠራት አለባቸው፡፡

– እውቀት የሌለው፣ መረጃ የማያገኝ ህዝብ፣ የተደራጀና የተቀናጀ አደረጃጀቶች የለለው ሕዝብ ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፡፡ ከፖለቲካ ድርጅቶች የሚጠየቀውና የሚጠበቀው የተናደደ ሕብረተሰብን መፍጠር ሳይሆን መረጃ የሚያገኝ፣ እውቀት ያለው፣ የተደራጀና ድርጅቶቹ የተቀናጁ ሕብረተሰብ መፍጠር ነው፡፡

– ስለሆነም የወደፊት የትግል አቅጣጫችን የማሳወቅ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የማደራጀትና፣ ድርጅቶችን የማቀናጀት ሥራን ማዕከል ያደረገ መሆን አለበት፡፡

3.2 ገዢውን ፓርቲ በተመለከተ፡-

– የትኛውም ገዢ መደብ ተገድዶ እንጂ በልመና፣ በመለማመጥ በፈቃደኝነት ህዝብ የሚፈልገውን ለውጥ አያመጣም፡፡ ገዢው ፓርቲ ለለውጥ የሚገደደው በሕዝባዊ ኃይል ብቻ ነው፡፡ ገዢውን ፓርቲ ለለውጥ የሚያስገድድው ህዝባዊ ሠፊ እንቅስቃሴ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ገዢውን ፓርቲ ለማስገደድ ህዝባዊ እንቅስቃሴ የሚፈጠርበትን መንገዶች መቀየስና በነሱ ላይ መሥራት የወደፊት የትግል አቅጣጫችን መሆን አለበት፡፡

3.3 የፓርቲ ሥርዓታችንን የመለወጥ ሥራ አንዱ የትግል አቅጣጫችን መሆን አለበት

– ይህም የሚሆነው ገዢው ፓርቲ የሚጠቀመውን Patronage (አባታዊነት) እና የሙስና (Corruption)ስልት የፓርቲዎች አባላት፣ ደጋፊዎችና አጠቃላይ ህዝቡ እንዲታገሉት ካደረግን ነው፡፡ ይህም አንድ የወደፊት የትግላችን አቅጣጫ ነው፡፡

– ከዚህ አኳያ አንዳድ ተቃዎሚ ፓርቲዎች ከኢህአዴግ የሚሰጣቸው ድጎማ የጥገኝነትና የጠባቂነት ባህልን የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ ሙሰኝነት መሆኑን እንዲረዱ በቀጣይነት ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡

3.4 ብልሹ የምርጫ ሥርዓትን መለወጥ የወደፊት የትግል አቅጣጫችን ማድረግ አለብን፡፡

– ዴሞክራሲ በምርጫዎች ዘመን መሀከልም ሆነ በምርጫ ወቅትም መስፈን ያለበት ነው፡፡ ስለሆነም የፖለቲካ ምህዳር እንዲስተካከል በቁርጠኝነትና በቀጣይነት መታገል ይኖርብናል፡፡

– ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ ተፈጥሮ ምርጫን በተመለከተ የተመጣጠነ (Proportional) የምርጫ ሥርዓት እንዲገነባ ለማድግ ሕገ-መንግሥቱ የሚሻሻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር መታገል አስፈላጊ ነው፡፡

– ከአጭር ጊዜ አኳያ የትግል አቅጣጫችን ለ2ዐዐ5 ምርጫ የተስተካከለ ምህዳር እንዲፈጠር መታገል ነው፡፡

3.5 ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መንቀሳቀስ

– ላገራችን ችግሮች መፍትሔ ለማፈላለግ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ እርቅ መጥራት አስፈላጊ ነው፡፡ የፖለቲካ ችግሮችን/ልዩነቶችን ለመፍታት አንድነት በፕሮግራሙ ያስቀመጠው አቅጣጫ ትክክል ነው፡፡ ስለሆነም ችግሮችን በሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በውይይትና በድርድር የመፍታትን ባህል የበለጠ መዳበር የትግላችን አቅጣጫ መሆን አለበት፡፡

ከአጭር ጊዜ አኳያ የመድረክ መፈጠር፣ የ11 ፓርቲዎች በቅርብ ጊዜ የፈጠሩት መቀራረብ፣ የ2ዐዐ5 ምርጫን በተመለከተ የ33 ፓርቲዎች አብሮ መሥራት መጀመር

የዚህ አቅጣጫ ጅማሮ ነው፡፡ ስለሆነም የዚህን ዓይነት እንቅስቃሴ ማበረታትና መደገፍ ይጠበቅብናል፡፡ በቅርብ ጊዜ አንድ ሀገራዊ የምክክር ኮንፍራንስ እንዲጠራ የሚጠይቅ ሃሳብ እየተጠናከረ መጥቶአል፡፡ ይህን ጥሪ መደገፍና ማዳበር ይጠበቅብናል፡፡

– ልዩነቶችን በጉልበትና በመሣሪያ ኃይል ለመፍታት መሥራት ይቅር፡፡

– ለሥልጣን፣ ለዝናና ለሀብት ብለን መከፋፈልን እናቁም፡፡

– ለውይይቶችና ለድርድሮች ቅድመ ሁኔታ አናስቀምጥ፡፡

– የማንበርከክ/የማስጎብደድ ፍላጎት ባህል ይቅር፡፡

– ፍፁማዊነትን አስወግደን ‹‹የልዩነት መኖር መብት ለዘላለም ይኑር››እንበል፡፡

– ለህዝብ ወሳኝነትና የሥልጣን ባለቤትነት ጠንክረን በቀጣይነት እንታገል፡፡

– የማጎብደድና የተንበርካቢነት ባህልን በጽናት እንታገል፡፡

– ደፋር እንሁን፡፡ መጥፎ የሆነውን ነገር ከማስወገድ አንቆጠብ፡፡ መጥፎውን እናስወግድ እንጂ አንለማመድ፡፡

3.6 የሠላማዊ ትግል ስልት ባንድ በኩል የፈሪዎች የትግል ስልት ነው ብለው የሚያጣጥሉ አሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሠላማዊ ትግል (Passivism) ነው ተብሎም ይወሰዳል፡፡ ነገር ግን የሠላማዊ ትግል ስልት ባግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ ትልቅ ውጤት የሚያስገኝ ነው፡፡ የሠላማዊ ትግል ስልት ባገራችን ገና ባግባቡ ጥቅም ላይ አልዋለም፡፡ ስለሆነም የወደፊት የትግል አቅጣጫችን ለውጥን ለማምጣት የሠላማዊ ትግል ስልትን ባግባቡ መጀመርና ማዳበር መሆን አለበት፡፡ ሠላማዊ ትግል ባግባቡ መካሄድ አለበት ሲባል ግን ሠፊ ዝግጅት እና ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ መረሳት የለበትም፡፡

3.7 ውጫዊ ኃይልን ከመጠበቅ ይልቅ በራስ መተማመንና የራስን ችግር ለመፍታት በራስ መንቀሳቀስ እንዲለመድ ለማድረግ መሥራት ሌላው የወደፊት በትግላችን ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም በሁሉም የሀገራችን የኃይማኖት ተቋማት ይህን በተመለከተ የአመለካከት ለውጥ መምጣት ያስፈልጋል፡፡ ቤተሰብ፣ ትምህርት ቤትና የመገናኛ ብዙሃንም ከዚህ አኳያ የማይናቅ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

የኔን ችግር ፍታልኝ ብሎ ከመፀለይ ችግሮቼን ራሴ ለመፍታት እንድችል ጉልበት ስጠኝ ብለን አምላክን መለመን ይኖርብናል፡፡

በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር

ለአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ክፍል

ለአባላት ትምህርታዊ ፕሮግራም የቀረበ ወቅታዊ የመነሻ ጽሁፍ

ህዳር 16 ቀን 2ዐዐ5 ዓም

አዲስ አበባ

Categories: Uncategorized

መቼም የመጀመርያውን ባቡር ያስገቡትን የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት አፍርሶ ባቡር እናስገባ ማለት የታሪክ ምጸት ነው፡፡ ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው፡፡

November 24, 2012 Leave a comment

መቼም የመጀመርያውን ባቡር ያስገቡትን የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት አፍርሶ ባቡር እናስገባ ማለት የታሪክ ምጸት ነው፡፡ ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው፡፡

እኛ እያልን ያለነው ሀገሪቱ ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ለምን ቅድመ ጥናት ሲካሄድ የእምነትና የሐውልት ቦታዎች ፤ የአባቶቻችን ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለኢትዮጵያ አሻራቸውን ያስቀመጡበት ቦታ ከግምት ውስጥ አይገባም ? ወይስ ከበስተጀርባ ሌላ ነገር አለ……?..

“አይጥ ለሞቷ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች” ይላል ያገሬ ሰው

Who is ruling Ethiopia? Ethiopians? If so how come

 the government is so keen to destroy the country’s century old historical places and statutes while it has been busy building statutes in the name of solders killed during the war with the Derg Regime? We can smell something behind. We cannot remain indifferent and silent when intolerable and arrogant things are coming.  Please read and share.
Categories: Uncategorized

እባካችሁ አባቴን ኣፈላልጉልኝ

November 14, 2012 Leave a comment

እባካችሁ አባቴን ኣፈላልጉልኝ መርሓዊት ተፈሪ ጥላሁን እባላለሁ። ተወልጄ ያደኩት በኤርትራ ዋና ከተማ በኣስመራ ነዉ። ኣሁንም እዝያዉ ክእናቴ ጋር እኖራለሁ። በእናቴ ኤርትራዊት በባቴ ኢትዮጵያዊት ነኝ። ኣባቴ እኔ ሳልወለድ ተለየኝ። ስለሆኔም ስለሱ የማዉቀዉ በጣም ጥቂቱን ብቻ ነዉ። ታሪኩ እንደሚከተለዉ ነዉ:: ኣባቴ ሻምበል ተፈሪ ጥላሁን በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ወታደር ነበር። በሰሜን ኤርትራ በነበረዉ በናዶዉ ግንባር የፋይናንስ ሃላፊ ነበር። ኣባቴና እናቴ ተጋብተው ብዙም ሳይቆዩ ይህ ኣባቴ የነበረበት የናዶዉ ግንባር በህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (በ EPLF) ይደመሰስና ኣባቴም በዚሁ ጦርነት ይማረካል። እስከ 1991 (የደርግ ዉድቀት ጊዜ) ከመሰሎቹ ጋር በሳሕል በረሓ በምርኮኞች ማቆያ ካምፕ ዉስጥ በሕይወት እንደነበር ሰምቻለሁ። እዚያም እያለ ለምርኮኞቹ የተለመደ ስራዉን (የስራዉ ስም ይቀየር እንጂ) የማከናወን ሓላፍነት በ EPLF ተሰጥተዉት ይሰራ እንደነበር ሰምቻለሁ። በ1991 ላይ ደርግ ስደመሰስ እነዚያ ምርኮኞች የፈለጉት ወደ ኢትዮጵያ ሌሎቹም ወደ ሱዳን እንደየምርጫቸዉ ተፈቅዶላቸዉ እንደተላኩና የተወሰኑትም እዚሁ ኤርትራ ለመቅረት ፈልገዉ እንደቀሩ ሰማሁ። ኣባቴ ግን ከ3ቱ ወገኖች የትኞቹን እንደመረጠና ምን እንዳጋጠመዉ እስካሁን የማዉቀዉ ነገር የለኝም። ባጭሩ ስለባቴ የማዉቃቸዉ ወይም የሰማሁዋቸዉ የሚከተሉትን ብቻ ናቸዉ። 1. ያባቴ ስም ሻምበል ተፈሪ ጥላሁን 2) የትዉልድ ቦታዉ ኣርሲ አሰላ 3) የሚናገረዉ ቋንቋ በብዛት ኣፋን ኦሮሞ (of course, ኣማሪኛንም) 4) የስራ ሓላፍነቱ የናደዉ እዝ የፋይናንስ ሃላፊ 5) የናደዉ እዝ ስደመሰስ ከሌሎች በርካታ የደርግ ወታደሮች ጋር በመሆን በ EPLF መማረኩን 6) እስከ 1991 በ EPLF የምርኮኞች ማቆያ ካምፕ ዉስጥ በሕይወት መቆየቱን 7) እዝያዉ የምርኮኞች ማቆያ ካምፕ ዉስጥም እያለ በተለመደ ስራዉ ምርኮኞቹን ስያገለግል መቆየቱን ነዉ። ስለ ኣባቴ ልያዉቁ ወይም ካሁኑም ብሆን በማፈላለጉ ላይ ልያግዙ ይችላሉ ብዬ የሚላቸዉ ዓይነት ሰዎች የሚከተሉት ናቸዉ። 1) በ1980ዎቹ ዓመታት ዉስጥ በናደዉ እዝ ተመድበዉ የነበሩ የደርግ ሠራዊት ኣባሎች በተለይም ከእነሱም ዉስጥ በፋይናንስ የስራ ዘርፍ ላይ ተመድበዉ ስሰሩ የነበሩ ሰዎች 2) የዉግያ ግንባሩ (ናደዉ እዝ) ስደመሰስ ተማርኮ ወደ ሳሕል በምርኮ የተወሰዱ የደርግ ጦር ኣባሎች 3) በትዉልድ ቦታቸዉ ልክ እንደ ኣባቴ ኣርሲ አሰላ ሆኖ በኤርትራ ሙሉ (በተለይም በናደዉ እዝ) በዚያን ጊዜ የነበሩ የደርግ ጦር ኣባሎች እንደነዚህ ዓይነቶቹን ሰዎች የሚታዉቁዋቸዉ እባካችህ ኣጠያይቃችሁ ስለ ኣባቴ ማንኛዉንም ዓይነት መረጃ ብታገኙ በዚህ የ facebook ኣድራሻ ወይም በኢመይል merertut@gmail.com በመላክ ተባበሩኝ። ማሳሰብያ እኔ ባሁኗ ሰዓት የእናቴን ሃገር ዜግነት ኣግኝቼ በሰላም ከሷ ጋር እየኖርኩ ነኝ። ኣባቴ እስከ ዛሬ በሕይወት ልኖርም ላይኖርም ይችላል። ያም ሆነ ይህ ኣሁን እኔ የሚፈልገዉ ሁለት ነገር ብቻ ነዉ። እነሱም 1) ያባቴን በሕይወት መኖር ኣለመኖር በእርግጠኝነት ከሚያዉቁት ሰዎች ሰምቼ ማረጋገጥ 2) ከምንም በላይ ደግሞ ያባቴን የተሟላ ማንነት ኣዉቄ በሕይወት ካሉት ያባቴ የስጋ ዘመዶች ጋር መተዋወቅ መልእክቴን ለሚታዉቁዋቸዉና ይህንን ጉዳይ ልያዉቁት ይችላሉ ብላችህ ለምታስቡዋቸዉ ሰዎች ሁሉ በማዳረስ ኣግዙኝ። ለሚታደርጉልኝ ቀና ትብብር ከልብ ኣመሰግናለሁ መርሓዊት ተፈሪ ጥላሁን ከኤርትራ፡ ኣስመራ

Categories: Uncategorized